የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኑክሌር ተቆጣጣሪ ዳይሬክተር ጄኔራል ዩኪያ አማኖ አረፉ

71
ኢዜአ ሀምሌ 15/2011የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ዩኪያ አማኖ በ72 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ኤጀንሲው አስታወቋል ሲሊ አናዶል ዘግቧል። የአለም አቀፍ የአቶምክ ኢነርጅ ኤጀንሲ ጸሐፊ በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ሆነው ዳይሬክተር ጄኔራል ዩኪያ አማኖ መሞታቸውን ገልፀዋል።
የአለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብም በመግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል። የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ፌደሪካ ሞጊርን በዳይሬክተር ጄኔራል ዩኪያ አማኖ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም ሁልጊዜ እጅግ ልዩ ችሎታቸውን እና ሙያቸውን በመጠቀም ከአድልዎ ነጻ በሆነ መንገድ አለም አቀፉን ማህበረሰብ በማገልገል ላይ እንደነበሩ በመግለፅ አብረው የሰሯቸው ስራዎች እንደማይረሱ ተናግረዋል። አብሪያቸው በመስራት ከፍተኛ የሆነ ደስታ እና ኩራት ይሰማኛል ሲሉ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ፌደሪካ ሞጊርን በትዊተር ገፃቸው አስነብበዋል። የተቋሙ ኃላፊ የነበሩት ሚስተር አማኖ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ እስከ ሰኔ 2009 የኤጀንሲው ዳይሬክተር ጄኔራል እስከሆኑበት ጊዜ ድረስ በኤጀንሲው የጃፓን ተወካይ የነበሩ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 1, 2009 ህይዎታቸው እስካለፈበት ድረስ የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ እንደነበር በመረጃው ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም