በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ36 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከሉ

64
አዲስ አበባ ሀምሌ 15/201  ከሁለት ሺህ በላይ ዜጎች በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ36 ሺህ በላይ ችግኞች ተከሉ። በዛሬው ዕለት በፓርኩ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የፌዴራልና የክልል ሥራ አመራሮች፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲዎች ተማሪዎች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሠራተኞች ተሳትፈዋል። ፓርኩ ባለፈው መጋቢት መጨረሻና ሚያዚያ ወር መጀመሪያ የሰደድ እሳት አደጋ ደርሶበት እንደነበር ይታወቃል። ዛሬ በፓርኩ የተካሄደው የችግኝ መትከል መርሃ-ግብር ፓርኩን መልሶ ለማልማት ከተያዙት ውጥኖች መካከል አንዱ ነው ተብሏል። ለችግኝ ተከላው የሚያስፈልጉ ጉድጓዶች ከአንድ ወር በፊት ተቆፍረው መዘጋጀታቸውም ነው የተገለጸው። ከፓርኩሥነ-ምህዳርጋርየሚስማሙስድስትአገርበቀልየችግኝአይነቶችየተተከሉሲሆን፤ከሁለት ሺህ በላ ይዜጎች በተከላው ላይተሳትፈዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም