ቀጥታ፡

በአማራ ክልል የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሰላም ማስፈንና ሕዝቡን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል--የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባዔ

ባህር ዳር ሐምሌ 15 / 2011 በአማራ ክልል የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሰላም ማስፈንና ሕዝቡ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አሳሰቡ። ምክርቤቱምሰኔ15/2011በተደረገውመፈንቅለመንግሥትሕይወታቸውንላጡየክልሉከፍተኛአመራሮችናለመከላከያሠራዊትጄኔራልመኮንኖችየሕሊናፀሎትበማድረግ 13ኛ መደበኛጉባዔውንጀምሯል። አፈ ጉባዔዋ ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ማሞ የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔው ሲጀመር እንደተናገሩት ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም አመራር በመስጠት ሰላምን ማስፈንና ልማቱን ማስቀጠል ይገባል። ለዚህም የሕግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያ አንድነት ቁርጠኛ አቋም ያለው፣ የማንንም መብትና ጥቅም የማይነካ በጋራ ልማት፣ በእኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ሰርቶ ለመበልጸግ ዓላማ አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ገልጸዋል። የአማራ ክልል ሕዝብ ከሁሉም ብሄሮች/ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ፣ ተዛምዶ፣ ተዋልዶና ተቻችሎ እንደሚኖር ያመለከቱት አፈ ጉባዔዋ፣ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት በሚፈጥሩት ውዥንብር በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሰ የሞት፣ የመፈናቀልና የንብረት ውድመት እየደረሰበት መሆኑን ተናግረዋል። በአማራ ጠል ትርክት በሕዝቦች አጀንዳቸው ባልሆነ ጉዳይ እርስ በእርሳቸው እንዲይቃቃሩ፣ በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በዘር፣ በቀበሌና በጎጥ፣ በመከፋፈል ለግጭት ማነሳሳትና ለጥፋት መሰለፍ ታሪካዊ ስህተት እንጂ፤ ጀግንነት አይደለም ሲሉም ወይዘሮ ሰሙወርቅ ተናግረዋል ። በክልሉናከክልሉውጭበተለያየጊዜየደረሱችግሮችተባብሰውእንዳይቀጥሉበተፈናቀሉናወገኖችላይየደረሰውንጉዳትበአካልሄዶበመወያየትምማስተካከያእንዲደረግየምክርቤትአባላትየክትትልናቁጥጥርተግባራትማከናወናቸውንገልጸዋል። በክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በመከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች በተፈጸመወ ግድያ የአማራ ክልልና የኢትዮጵያ ሕዝብን ይዘን በመፅናናትና ቁርጠኝነትን በመላበስ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረቱ እንደሚቀጥል አፈ ጉባዔዋ አረጋግጠዋል። የክልሉ ሕዝብ አስተዋይ፣ ትግስተኛ፣ አገር ወዳድና ሕዝብ አክባሪ በመሆን ኅዘኑን ኅዘናቸው በማድረግ ዳግም ሌላ ኪሳራ እንዳይመጣ ሰላም እንዲሰፍን መንግሥትና ሕዝብ እንዲረጋጉ በመስራታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአማራ ክልል ጥቃትን የራሳቸው በማድረግ ላሳዩት ወገንተኝነትም አፈ ጉባዔዋ አመስግነዋል። ምክር ቤቱ ለአራት ቀናት በሚያደርገው ቆይታም በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም