ቀጥታ፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ቀመርን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ አድርጎ አሻሻለ

አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 18/2011 የፌዴሬሽን ምክር ቤት ላለፉት 21 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ቀመርን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ አድርጎ አሻሻለ። በ1987ዓ.ምየጸደቀውንህገመንግስትተከትሎየፌዴሬሽንምክርቤትበኢትዮጵያየፖለቲካታሪክየመጀመሪያየሆነውንናእስከአሁንድረስበስራላይየዋለውንቀመርአዘጋጅቷል። በተዘጋጀውቀመርመሰረትበፌዴራልመንግስትናበክልልመንግስታትመካከልየጋራገቢዎችአስተዳደርናክፍፍልሲያደርግቆይቷል። በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 98 ስለ ፌዴራል መንግስትና ክልሎች የጋራ የታክስና ግብር ስልጣን ተደንግጓል። ምክር ቤቱ በ5ኛው የፓርላማ ዘመን 4ኛ ዓመት የስራ ጊዜ ሰኔ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላለፉት 21 ዓመታት አገልግሎት ላይ የነበረውን የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ቀመር እንዲሻሻል ውሳኔ አሳልፏል። በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የገቢ ክፍፍልና የክልሎች የተመጣጠነ ዕድገት ጥናት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በስራ ላይ የነበረው የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ቀመር በተለያየ ምክንያት ማሻሻያ አስፈልጎታል። ክልሎች በቀመሩ መሰረት ገቢያቸውን እያገኙ እንዳልሆነ መግለጻቸውና ይህም በመረጃ መረጋገጡ እንዲሁም ቀመሩ ከወቅቱ ጋር አብሮ የሚሄድ ሆኖ መስተካከልያለበት በመሆኑ ቀመሩን ማሻሻል እንዳስፈለገ ጠቁመዋል። እንደ አቶ ያዕቆብ ገለጻ፤ ቀመሩን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ተገቢው ድልድል ለተገቢው የመንግስት አካል እንዲደርስ ለማስቻል ነው። እንዲሁምበፌዴራልመንግስትበኩልየወጡየገቢደንቦችበጋራገቢዎችክፍፍልመስፈርትላይአሉታዊተፅዕኖአሳድረውእንደነበረምአስረድተዋል። ከዚህበፊትየነበረውየጋራገቢዎችአስተዳደርናክፍፍልቀመርአብላጫውንለፌዴራልመንግስትገቢእንዲሆንየሚፈቅድመሆኑንአቶያዕቆብገልጸዋል። ከልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የትርፍ ግብር፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከኤክሳይስ ታክስ የሚሰበሰቡ ገቢዎች አብላጫውን የፌዴራል መንግስት እንዲወስድ የሚፈቅድ እንደነበር አስታውሰዋል። ከከፍተኛማዕድን፣ጋዝናፔትሮሊየምስራዎችየሚሰበሰብየሮያሊቲገቢ 60 በመቶለፌዴራልመንግስትገቢእንዲሆንሀብቱለመነጨበትክልልደግሞ 40 በመቶክፍፍልእንዲደረግቀደምሲልበነበረውቀመርእንዳለአመልክተዋል። በስራ ላይ የነበረው የጋራ ገቢ ክፍፍል ቀመር በክልሎች መካከል ፍትሃዊነትን የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ ምክር ቤቱ ሰኔ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው እንዲሻሻል ውሳኔ ማሳለፉን አቶ ያዕቆብ ተናግረዋል። በተሻሻለውየጋራገቢክፍፍልቀመርመሰረትየፌዴራልመንግስትናክልሎችበጋራከሚያቋቁሟቸውየልማትድርጅቶችየሚሰበሰበውየትርፍግብር 50 በመቶገቢውለመነጨበትክልልእንዲሆንቀሪው 50 በመቶደግሞለፌዴራልመንግስትገቢእንዲሆንተወስኗል። የፌዴራልመንግስትናክልሎችበጋራከሚያቋቁሟቸውየልማትድርጅቶችየሚሰበሰበውየስራግብርገቢሙሉበሙሉገቢውለመነጨበትክልልእንዲሆንተደርጓል። በህገመንግስቱየጋራገቢከሚባሉትቀጥተኛያልሆኑታክሶችማለትምከተጨማሪእሴትታክስናከኤክሳይስታክስየሚገኘውገቢ 50 በመቶለሁሉምክልሎችእንዲሁምሌላው50በመቶለፌዴራልመንግስትገቢእንዲሆንየተደረገሲሆንየክልሎችድርሻበመካከላቸውጥቅልዓላማባለውየማመጣጠኛድጎማቀመርመሰረትእንዲከፋፈሉምክርቤቱውሳኔአሳልፏል። በአዲሱ ቀመር ከድርጅቶች የሚሰበሰብ የትርፍ ግብርና የባለ አክሲዮኖች ትርፍ ግብር 50 በመቶ ገቢው ለመነጨበት ክልል ገቢ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ቀሪው 50 በመቶ ለፌዴራል መንግስት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል። ከከፍተኛ ማዕድን፣ ጋዝና ፔትሮሊየም ስራዎች የሚሰበሰብ የሮያሊቲ ገቢ 25 በመቶ ለፌዴራል መንግስት፣ 25 በመቶ ገቢ ደግሞ ሀብቱ ላልመነጨባቸው ክልሎች እንዲሁም 50 በመቶ ገቢ ሀብቱ ለመነጨበት ክልል ሆኖ ከዚህ ውስጥ 10 በመቶ ገቢ ሀብቱ ለመነጨበት የአካባቢ አስተዳደር በክልሉ አማካይነት እንዲተላለፍ ምክር ቤቱ ወስኗል። በክልሎች መካከል ያልተጣጠነ ልማት ሊያስከትል የሚችል ከፍተኛ የሆነ ገቢ የሚያስገኝ ነገር ከተከሰተ ቀመሩ ሊከለስ የሚችልበት ዕድል መኖሩን አቶ ያዕቆብ ጠቁመዋል። በፌዴሬሽን ምክር ቤት የፀደቀው አዲሱ የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ቀመር በስራ ላይ የሚውለው ከ2013 የበጀት ዓመት ጀምሮ ነው።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም