ቀጥታ፡

ፍርድ ቤቱ አሰራሩን በማቀላጠፍ ከ6 ሺህ ለሚበልጡ የክስ መዝገቦች ውሳኔ ሰጠ

ዲላ ሐምሌ 09/2011 የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሰራሩን በማዘመን በአጫጭር ቀጠሮዎች ለ6 ሺህ 796 መዝገቦች ውሳኔ መስጠቱን ገለፀ ። የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ፈቃዱ እንዳሉት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እራሱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማደራጀት ቀናትን የሚጠይቁ አገልግሎቶችን በደቂቃዎች መጨረስ የሚያስችለውን አስራር ዘርግቷል ። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፈጣን፣ ተደራሽና ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት ለመስጠት የተደረገው ጥረት ውጤታማ አድርጎታል ። በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ፍርድ ቤቶች ከቀረቡት 7 ሺህ 130 መዝገቦች ውስጥ 6 ሺህ 796 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን አብራርተዋል። አፈጻጸሙ 95 በመቶ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ4 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ። ውሳኔ ከተላለፋባቸው መዝገቦች መካከል 5 ሺህ 881 መዝገቦች ከሁለትወርባነሰጊዜውስጥውሳኔማግኘታቸውንምያስረዱትአቶሳሙኤል "በፍርድቤቶችየአገልግሎትአሰጣጥቅልጥፍናንለማሳደግበተደረገውጥረትየተገኘውጤትነው" ብለዋል ፍርድ ቤቱ በሙስና ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ ፣ በሴቶች ጥቃትና መሰል ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አስረድተዋል ። ፍርድ ቤቱ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግና ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ድጋፍ በማግኘት ከልማዳዊ አሰራር ተላቆ ወደ ዲጂታል አሰራር በመሸጋገሩ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደቻለ ተናግረዋል ። ዘመናዊ አሰራሩ የተገልጋዩን ህብረተሰብ ክፍል የጊዜና ገንዘብ ብክነት ከማዳኑ ባሻገር የመዝገብ መሰወርና መጥፋትን ሙሉ በሙሉ ማሰቀረቱን አስረድተዋል። በ2012 የስራ ዘመንም ህብረተሰቡን በበለጠ መልኩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆንና የመዝገቦችን ዝውውር ዲጂታል ለማድረግ "ወረዳ ኔትና ኢ- ፋይሊንግ" የተባለ አገልግሎት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል። የይርጋጨፌ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ እሱባለው ማሞ በበኩላቸው" በፍርድ ቤቱ የሚመጡ ጉዳዮች በመጡበት ዓመት ውሳኔ እንዲያገኙ ጥረት ይደረጋል "ብለዋል ። በወረዳው የሚመጡ መዝገቦች ቁጥርና ያለው የሰው ኃይል ብዛት እንደማይጣጣም አመልክተው አንድ ዳኛ በተዘዋዋሪና በመደበኛ ችሎት እስከ 300 የሚደርሱ መዝገቦች ለማየት የሚገደዱበት አጋጣሚ መኖሩን ጠቁመዋል። የዲጂታል አሰራሩን ተደራሽ በማድረግ ጫናውን ይቀነሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም አመልክተዋል። የይርጋ ጨፌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ናዝሬት ሽፈራው በሰጡት አስተያየት የነበራቸው ጉዳይን ለፍርድ ቤት ባቀረቡ ሁለት ወራት ውስጥ ውሳኔ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የነበረው የተንዛዛ አሰራር ተቀይሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ መስጠት መቻሉ እንዳስደሰታቸው ጠቁመዋል። ሌላው የዚሁ አካባቢ ነዋሪ ወይዘሮ ሃይማኖት ታደሰ በበኩላቸው ውል ይከበረልኝ በሚል ክርክር ያቀረቡት አቤቱታ በአንድ ወር ውስጥ ውሳኔ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ፍርድ ቤቶች ጉዳዮችን የማጥራት አቅማቸውና ጊዜ አጠቃቀማቸው እየተሻሻለ መምጣቱን አስረድተዋል። በዞኑ በ23 ተዘዋዋሪና በዘጠኝ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስራው እንደሚካሄድ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክቷል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም