ከዛሬ 75 አመት በፊት ተሰርቆ የነበረው ቦርሳ ለባለቤቷ ተመልሷል

46
ኢዜአ ሀምሌ 10/2011 በአሜሪካ ኤሊኖስ ግዛት ነዋሪ የሆኑት  የ89 ዓመት አረጋዊት ተሰርቆባቸው የነበረን የኪስ ቦርሳ ከ75 ዓመት በኋላ በእጃቸው እንዲገባ መደረጉን ዩ ፒ አይ ያልተጠበቀና አስገራሚ ነው ሲል በፊት ገፁ አስነብቧል፡፡ እንደ ዘገባው የኪስ ቦርሳው የተገኘው ጥገና በሚደረግለት ሴንትሪላ በተባለ ሃይማኖታዊ ትምህርት ቤት የሴቶች መፀዳጃ ቤት ለዕድሳት በሚል የማፍረስ ተግባር ሲከናወን እንደሆነ ቄስ ሴዝ ባልትዜል የተባሉ የት/ቤቱ ሃላፊ ተናግረዋል። የኪስ ቦርሳዎቹ በውስጣቸው ገንዘቦችን እንዲሁም እኤአ በ1940ዎቹ አጋማሽ ተማሪ የነበሩ ሰዎች መታወቂያዎችን ይዘው እንደተገኙና ከዋሌት ቦርሳ ውስጥ የተገኙትን መታወቂያዎች ማህበራዊ ሚዲያ (ፌስ ቡክ) ላይ እንዲጫኑ ማድረጋቸውን ቄስ ባልትዜል ተናግረዋል። ‘ምናልባት መታወቂያ ላይ ያሉት ሰዎች ቤተ ዘመዶች መጥተው እንዲወስዱ በሚል ነበር መታወቂያዎቹን ፌስ ቡክ ላይ የጫንኩት፤ ጊዜው ረጅም በመሆኑ የመታወቂያውን ባለቤቶች በህይወት ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላልና” በማለት ቄስ ባልትዜል አክለዋል። ባለፉት 75 ወይም 100 ዓመታት ማንም ስው አይቶት የማያወቀው ነገር ብቅ ይላል ብሎ ስጠብቅ እንደነበር  ባልትዜል ለሲ ኤን ኤን ተናግሯል። ከኬ ኤስ ዲ ኬ ቲቪ አንድ አስገራሚ ዜና ተሰማ እሱም በፌስ ቡክ ምስላቸው ከተለቀቁት ሰዎች ቤቲ ሲሶም የተባሉ የ89 አመት ሴት አረጋዊ ሴይንት ሉዊዝ በተባለ ቦታ እየኖሩ እንደሆነ ቄስ ባልትዜልም በሁኔታው መገረማቸውን ተናግረዋል። ከዛሬ 75 አመታት በፊት ከተሰረቀባቸው ብጭቅጫቂ ቀይ የኪስ ቦርሳ ጋር መገናኘታቸው ሲሶምን በእጅጉ አስገርሟቸዋል። "የተሰረቀው ቦርሳዬን ይኖራል ብዬ ከማላስበው ቦታ (መፀዳጃ ቤት ውስጥ ባለ ክፍት ቦታ) ላይ ማግኘቴ ልገምተው የማልችለው ነገር ነው።" ሲሉ ሲሶም ተናግረዋል። ቦርሳውን እንደተረከቡ አንድ እጅግ የሚፈልጉት አንዳች ነገር በውስጡ ማግኘት መቻላቸው እንዳስደሰታቸው የተናገሩ ሲሆን በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የተሰዋው ወንድማቸውን ፎቶ ትልቅ ነገር ብለውታል። "ፎቶውን ሳገኘው እጅግ ደስተኛ ነበርኩ፤ ምክንያቱም ወንድሜን የማስታውስበት ፎቶ እጄ ላይ አልነበረምና" ብለዋል ሲሶም ለዩ ፒ አይ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም