ቀጥታ፡

ህብረተሰቡ ለሰላም ዘብ እንዲቆም የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ

መቱ  ሀምሌ 9/ 2011  ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን  የለውጥ እንቅስቃሴ በማስቀጠል ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ህብረተሰቡ ሰላሙን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባው የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ። የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የአጋሮ ከተማ አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት የሰላምና ልማት ኮንፍረንስ ትናንት በአጋሮ ከተማ ተካሄዷል። በኮንፍራንሱ ላይ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዳስገነዘቡት በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት እንዲረጋገጥ በኢትዮጵያውያን ገንቢ ፣ባህላዊና ታሪካዊ ቱውፊቶች ላይ የተመሰረተ የሰላም ግንባታ ተግባር በዘላቂነት ማስቀጠል ይገባል ። ሁሉም ዜጎች በመደማመጥ ፣ በመከባበር፣ በአብሮነት፣በፍትህና በይቅርታ ለሀገሪቱ ሰላም ግንባታ ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ”ኢትዮጵያ ልዩነታቸውን በጸጋ ተቀብለውና አክብረው በሰላም አብረው የሚኖሩ ቅን ህዝቦች ሀገር ናት” ያሉት ቀሲስ ታጋይ እሴቶቻችንን ለማጥፋት የሚታትሩ አካላትን ሴራ በመጠየፍና በማውገዝ መላው ህዝብ ለአብሮነትና ለሰላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የኦሮሚያክልልየኃይማኖትተቋማትጉባኤዋናጸሐፊፓስተርቦጃ  አመንቲበበኩላቸውበተለይገናለማደግበጥረትላይባለችሀገርከሁሉምነገርአስቀድሞመረጋገጥያለበትሰላምመሆኑንገልጸዋል። ”እያንዳንዱ ዜጋ ከቤቱ ውስጥ ጀምሮ ለሰላም መስፈን ጥረት ማድረግ አለበት” ያሉት ፓስተር ቦጃ የሀገር ልማትና እድገት የሚረጋገጠው እያንዳንዱ ዜጋ ለሰላም በሚሰጠው ዋጋ ልክ እንደሆነ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጎማ ወረዳና የአጋሮ ከተማ ቤተ ክህነት ኃላፊ ቄስ መላአከ ገነት ካሴ የሀገሪቱን ሰላም ለማናጋትና የህዝቦችን የአብሮነት ባህል ለመሸርሸር የሚጥሩ አካላት ቢኖሩም ህዝቡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በሁሉም የእምነት ተቋማት የሚሰበከውን ሰላም ህብረተሰቡ በልቡ በማኖር ተግባራዊ እንዲያደርገው ያሳሰቡት ደግሞ የአጋሮ ከተማ መስጊድ ኢማም ሼህ ሀቢብ ሁሴን ናቸው። ህዝቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተለያዩ ወቅቶች ለሚናገሯቸው የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት መልዕክቶች ትልቅ ዋጋ በመስጠት ለሀገሩ ሰላምና እድገት የሚጠበቅበትን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በኮንፈረንሱ ከፌዴራልና ከክልል የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንዲሁም ከአጋሮ ከተማና ጎማ ወረዳ የተወጣጡ የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም