የምስራቅ ወለጋ ዞን ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በእሳት ቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት

75
ነቀምቴ ሰኔ 4/2010 በነቀምቴ ከተማ የሚገኘው የምስራቅ ወለጋ ዞን ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ትናንት ሌሊት በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ ጉዳት እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል፡፡ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወረዳ አንድ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አለማየሁ እምሩ ለኢዜአ እንደገለጹት በጽህፈት ቤቱ ውስጥ ሌሊት ስምንት ሰዓት ተኩል የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ቢሮውን ከነውስጥ ንብረቱ አውድሟል፡፡ ለሁለት ሰዓት ያህል የቀጠለው የእሳት ቃጠሎው በአቅራቢው ወደ ሚገኘው የነቀምቴ ሆስፒታል እንዳይዛመት የጸጥታ ኃይሎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር መቻሉን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ የአደጋው መንስኤና የወደመው ንብረት ግምት የሚያጣራ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን አስታውቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም