የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9637 ተማሪዎች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9637 ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ ሀምሌ 6/2011 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9637 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው በ10 ኮሌጆችና 12 ትምህርት ቤቶቹ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 9637 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 2763 ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል። ዩኒቨርሲቲው 5876 ተማዎችን በቅድመ ምረቃ ፣ የቀሩትን 3761 ተማሪዎችን ደግሞ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 230ዎቹ በሶስተኛ ድግሪ የተመረቁ ናቸው። ከእነዚህም 2085 ተማሪዎችን በማታ ፕሮግራም፣ 319 ተማሪዎችን በርቀት እንዲሁም 1995 ተማሪዎችን ደግሞ በክረምት ፕሮግራም ነው አሰልጥኖ ዛሬ ያስመረቀው። በተጨማሪም ለአገሪቷ ሰፊ ግልጋሎት በመስጠት ለሚታወቁት ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንዲሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም የክብር ዶክተሬት ማዕረግ ሰጥቷል። በዘንድሮው የትምህርት ዘመን አጠቃላይ ከ32 ዩኒቨርሲቲዎች 120 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመረቁም ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።