"ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም በደቡብ ኮሪያውያን ልብ ዘንድ ልዩ ቦታ አላት" የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ኪዮ ዋ - ኢዜአ አማርኛ
"ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም በደቡብ ኮሪያውያን ልብ ዘንድ ልዩ ቦታ አላት" የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ኪዮ ዋ
አዲስ አበባ ሀምሌ 3/2011 "ኢትዮጵያ ሁልግዜም በደቡብ ኮሪያውያን ልብ ዘንድ ልዩ ቦታ አላት" ሲሉ የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስ ካንግ ኪዮ ዋ ገለጹ። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስ ካንግ ኪዮ ዋን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስ ካንግ ኪዮ ዋ ኢትዮጵያ በታሪክ የደቡብ ኮሪያ የቅርብ አጋር እንደሆነችና እ.አ.አ በ1950 መጀመሪያ አካባቢ በነበረው በኮሪያ ጦርነት ወቅት የጦር አባላቶቿን በማዝመት ያከናወነችው ተግባር መቼም ቢሆን የማይረሳ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት "ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም ቢሆን በደቡብ ኮሪያውያን ልብ ልዩ ቦታ አላት" ሲሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። የልማት ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም የደቡብ ኮሪያ ዋንኛ አጋር እንደሆነችና ይሄንንም አጋርነት ደቡብ ኮሪያ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደምትሰራ ተናግረዋል። ደቡብ ኮሪያ የልማት አጋርነቱን ወደ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትብብር ማጠናከር ከፍ ለማድረግ እንደምትፈልግና የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን መፈራረም ትብብሩን ለማስፋት ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል አንዱ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል። የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱም የማድረግ ስራ እንደሚከናወንም አመልክተዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ትብብር እንዲያድግ የሚያስችሉ ተቋማዊ መዋቅሮችን መዘርጋት ሌላው በሁለቱ አገሮች የሚከናወን ተግባር እንደሆነ ነው ሚስ ካንግ ኪዮ ዋ ያስረዱት። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ውስጥ ለረጅም ጊዜ አብረዋቸው የሰሩት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለአገሪቱ ትልቅ ውጤት እንደሚያመጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሁለቱ መሪዎች ባላቸው የቀረበ ግንኙነትና የአገሮቹን የረጅም ጊዜ ግንኙነት በመጠቀም አገሮቹ በዓለም አቀፍ መድረክ ባላቸው የሚጋሯቸው አቋሞችና እሴቶች ይበልጥ እንዲጎለብት እንደሚደረግም ገልጸዋል። አገሮቹ በአሁኑ ሰአት ብዙ የሚጋሯቸው ነገሮች እንዳሉና አሁን ያለው ወቅት ለሁለትዮሽ ግንኙነት በጣም ልዩ ጊዜ እንደሆነም አክለዋል። የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የፕሮቶኮልና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸብር ጌትነት ሁለቱ መሪዎች የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ይበልጥ ግንኙነታቸው ሊጠናከሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ተናግረዋል። ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው በአገሮች መካከል ሊኖረው ከሚችለው ግንኙነት ባለፈ በደም የተሳሰረና እጅግ በጣም ጥብቅ እንደሆነ በውይይታቸው ወቅት መነሳቱን ገልጸዋል። ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ በጤና፣ በትምህርት፣ በሳይንስ እና በሌሎች መስኮች ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች መሆኑ ነው ያሉት አቶ አሸብር በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች የሚውል በረጀም ጊዜ የሚከፈልና አነስተኛ ወለድ ያለው የ300 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረሟን ጠቅሰዋል። አሁን በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ታሪካዊነቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ፊት እንዴት እየጎለበተ እያደገ መምጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉንም ጠቅሰዋል። የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማዳበር የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ፕሬዚደንቷ መግለጻቸውንና የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሊሳተፉባቸው የሚችሉ በርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዳሉና ወደ ኢትዮጵያ ባለሀብቶቹ መጥተው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለም መግለጻቸውንም የፕሮቶኮልና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ኪዮ ዋ ዛሬ ረፋድ ላይ ከኢትዮጵያ አቻቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የሁለትዮሽ ትብብሩን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እ.አ.አ በ1963 ነው