የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አሳሰበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አሳሰበ
ሐምሌ 3/2011 የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የማሳሰቢያ መልዕክት አስተላለፈ። ባለስልጣኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአዲስ አበባ ከተማ በ57 የምግብ ምርት ዓይነቶች ላይ በተደረገ የገበያ ጥናት የከረሜላ፣ የገበታ ጨው፣ የማር፣ የለውዝ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ የህጻናት ምግብ፣ የቪምቶና የአቼቶ ምርቶች ላይ መሰረታዊ ችግር ተገኝቶባቸዋል። የምርት ዓይነቶቹ መሰረታዊ የገላጭ ጽሁፍ ክፍተት፣ የሚመረቱበት ቦታ፣ የንጥረ ነገር ይዘት አለመኖርና አምራች ድርጅቶቻቸው የማይታወቁ እንደሆነ አመልክቷል። ምርቶቹ የመጠቀሚያ ጊዜ ማብቂያው የማይታወቅ መሆኑንም እንዳረጋገጠ ባለስልጣኑ ገልጿል። ባለስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቁሟል። ህብረተሰቡ ማንኛውንም የምርት ዓይነት ሲገዛ ምርቱ የተመረተበትና የመጠቀሚያ የአገልግሎት ጊዜው ትክክለኛነት፣ ያልተፋቀና ያልተሰረዘ መሆኑን፣ የአምራች ድርጅቱ ሙሉ አድራሻ፣ የምርት መለያ ቁጥር ያለውና የብሔራዊ የደረጃ ምልክት የለጠፈ መሆኑን በማረጋገጥ መግዛት እንዳለበት አስገንዝቧል። ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የታገዱትን ምርቶች ህብረተሰቡ ገበያ ላይ ካገኛቸው በአቅራቢያ ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላትና በባለስልጣኑ ነጻ የስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ተጠይቋል። ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው በሚል የለያቸው የምግብ ምርት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡- 1.ጆሊ ሎሊፖፕ 2.አናናስ ከረሜላ 3.ኮላስ ከረሜላ 4.ኦሊ ፖፕ 5.ቤስት ከረሜላ 6.የስ ከረሜላ(ኮፊ ከረሜላ) 7.ማሚ ሎሊፖፕ 8.ሳራ ከረሜላ 9.ጃር ሎሊፖፕ 10.ጸሐይ ሎሊ ሎፕ 11.ዩኒክ ሎሊ ፖፕ 12.እንጆሪ ከረሜላ 13.ብርቱካን ከረሜላ 14.ይናቱ ሎሊ ፖፕ 15.ሀላዋ ከረሜላ አምራች ምርት 16.አፍያ የተፈጥሮ ማር 17.ሪትም ማር 18.በላይ ማር 19.ዊዲ የገበታ ጨው 20.ሱላ የገበታ ጨው 21.ናይ የገበታ ጨው 22.ሀያት የገበታ ጨው 23.አቤት የገበታ ጨው 24.በአምነት የገበታ ጨው 25.እናት የገበታ ጨው 26.አባይ ገበታ ጨው 27.አባት ገበታ ጨው. 28.ሴፍ አዮዳይድ ጨው 29.ጣዕም የገበታ ጨው 30.ደስታ የለውዝ ቅቤ 31.አስነብ የለውዝ ቅቤ 32.ኑኑ የለውዝ ቅቤ 33.አቢሲኒያ የኦቾሎኒ ቅቤ 34.ብስራት ለውዝ 35.ፈሌ የለውዝ ቅቤ 36.ሳባ የለውዝ ቅቤ 37.አዳ የለውዝ ቅቤ 38.አደይ አበባ የምግብ ዘይት 39.ቀመር የኑግ ዘይት 40.ምሳሌ የህጻናት ምግብ 41.ኤልሞ የልጆች መግብ 42.ሂሩት የህጻናት አጃ 43.ዘይነብ የህጻናት አጥሚት 44.ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት 45.ተወዳጅ የህናት ሽሮ 46.ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ 47.ዴኮ ቪንቶ 48.እስፔሻል ቪምቶ 49.ዳና ቪምቶ 50.ቃና ቪምቶ 51.ላራ ቪምቶ 52.ዛጎል አቼቶ 53.ናይስ አቼቶ 54.አምቴሳ አቼቶ 55.ማይ አቼቶ 56.መስ አቼቶ 57.ቫይኪንግ አቼቶ