የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎችን የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀት ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎችን የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀት ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ሀምሌ 3/2011 ኢዜአ የኢትዮጵያ የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎችን ዓለም አቀፉ የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀት ክፍተት ለመሙላት ጥረት መጀመሩን የሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህበር ገለፀ። የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህብር ዓለም አቀፍ የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ያሰለጠናቸውን ከ450 በላይ የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች አስመርቋል። የማህበሩ ፕሬዘዳንት አቶ ዩሃንስ ንጋቱ እንደገለጹት በኢትዮጵያ አለም አቀፉን የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና ትግበራ ላይ ብዙ ጊዜ የባለሙያዎች የእውቀትና ልምድ ማነስ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች የማኔጅመንት ውሳኔ ፈጣን አለመሆን፤ መረጃ በተደራጀ መልኩ አለመያዝ ክፍተት እንደሚስተዋልባቸውም አንስተዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ተከታታይ የሞያ ማሻሻያ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የገንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ ማድረግም ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። በገቢዎችሚኒስተርየታክስናኦዲትዳይሬክተርአቶብርሃኑአበበም ስልጠናው በዓለምአቀፍየፋይናስ አዘገጃጀትናትግበራላይ ይስተዋሉ የነበሩትን ክፍተቶች ይሞላል ብለዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው ሰልጣኞች እንደገለጹት ለ20 ቀናት የተሰጣቸው ሞያዊ ስልጠና የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበት መልካም አጋጣሚ ነበር። በስልጠናው አዳዲስ አሰራሮችን እንዲከተሉም እውቀት ያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል።