ቀጥታ፡

አምባሳደር ደዋኖ ከድር ከጃፓን ባለኃብቶቸ ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 2/2011 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ደዋኖ ከድር የጃፓን ባለኃብቶችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ አምባሳደር ደዋኖ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያና ጃፓን መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ፤ የጃፓን ባለኃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም በስፋት እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። መንግስት በኢትዮጵያ መዋእለንዋያቸውን በማፍሰስ የመስራት ፍላጎት ላላቸው ባለኃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አምባሳደሩ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትምባሆ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የልኡካን ቡድኑን የመሩት ሚስተር ማሳሚቺ ቴራባታኪ በበኩላቸው ኩባንያው በኢትዮጵያ በትምባሆ ምርትና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ያለውን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የትምባሆ ቅጠል በስፋት ለማምረትና ወደ ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ  እንደሚሰሩ አስረድተዋል። ሚስተር ማሳሚቺ የኢትዮጵያ መንግስት የውጪ ኢንቨስተሮችን ለማበረታታት እያደረገ  ስላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም