በመተከል ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 14 ደረሰ

62
አሶሳ/ኢዜአ/ ሃምሌ2/2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ከሁለት ቀናት በፊት በተከሰተ ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 14 ደረሰ፡፡ የክልሉ ሠላም ግንባታ አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባዬታ ለኢዜአ እንዳሉት ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በወረዳው ገነተ ማርያም ቀበሌ በተከሰተ ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ 14 ደርሷል፡፡ ከተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ በቀበሌው የግብርና ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ግለሰብ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡ በገነተ ማርያም ቀበሌ ተከስቶ በነበረው ግጭት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ በ11 ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ኢዜአ መዘገቡ ያታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም