ቀጥታ፡

መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ ኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ሻምፒዮና ሆነ

መቀሌ ሰኔ 30/2011 መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ሻምፒዮና ሆነ። ክለቡ የዓመቱ ሻምፒዮና ለመሆን የበቃው ዛሬ በሜዳው ድሬዳዋን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት በማሸነፉ ነው። በተመሳሳይ ስሁል ሽረ በሜዳው ከፋሲል ከነማ ጋርእኩል አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት በመለያየቱ ለመቐለ 70 እንደርታ ማሸነፍ አስተዋጽኦ አድርጓል። የመቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ በወንዶች ፕሪሜየር ሊግ ውድድሩ ሻምፒዮና በመሆኑ የወርቅ ሚዳሊያና ዋንጫ ክዕለቱ የክብር እንግዳ ከአቶ ተስፋዬ ኦሜጋ ተበርክቶለታል። ዛሬ ውድድሩ የተካሄደበት የመቐለ ዓለም አቀፍ ስታድዮም በደጋፊና በተመልካች ብዛት ተጨናንቆ አልፏል። የመቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በሰጡት አስትያየት የዓመት ሙሉ ልፋታቸው ውጤት ዋጋ በማግኘቱ ደስታቸው ወሰን እንደሌለው ለኢዜአ ተናግረዋል። በአሁኑሰዓትየመቐለከተማየስፖርትደጋፊዎችበተከማውዋናዋናመንገዶችበመዘዋወርደስታቸውንእየገለፁይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም