የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ከ 3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ከ 3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2011የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 282 ተማሪዎች አስመረቀ። በአዲስአበባኮከብአዳራሽበተካሄደውየምረቃስነስርዓትላይየአዲስአበባከተማአስተዳደርምክትልከንቲባኢንጂርእንዳወቅአብጤንጨምሮተጋባዥእንግዶችናየዩኒቨርሲቲውየሴኔትአባላትተገኝተዋል። ትምህርታቸውን አጠናቀው ዛሬ ለምረቃ የበቁት በመደበኛ፣ በማታና በክረምት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በዲፕሎማና በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል። ታሪክና ቅርስ አስተዳደር፣ ቋንቋና ስነ-ጹሁፍ፣ ስነ ዜጋ፣ የቢዝነዝ አስተዳደር፣ የሕብረተሰብ ሳይንስ፣ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ፣ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ከስልጠና መርሃ ግብሮቹ መካከል ናቸው። በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፤ ዩኒቨርሲቲው በአዲስ መልክ ሜትሮፖሊታን ሆኖ ከተቋቋመ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ሲያስመርቅ በአጠቃላይ ለ60 ጊዜ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል።
በዚህም 70 ሺህ ተማሪዎች በማስመረቅ ሕብረተሰቡን በተለያዩ የሙያ መስኮች እንዲያገለግሉ ያስቻለ መሆኑ ተገልጿል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ሜትሮፖሊታን ሆኖ እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወዲህ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች ተማሪዎች ተቀብሎ እያሰለጠ በመሆኑ በመዲናዋ የሚታየውን የሰው ኃይል እጥረት እያቃለለ ነው። ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ለማህበረሰብ አቀፍ ልማትና ምርምር ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በተለይም ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትንንሽ እስከ መሰረታዊና ትልልቅ ጉዳዮች ድረስ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ችግሮች እንዲፈቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመሆኑ ተናግረዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፤ ተመራቂዎች በትምህረት ቆይታቸው በማህበራዊ ሚዲያ የሚስተጋባውን አሉባልታ ወደ ጎን በመተው የዩኒቨርሲቲውንና የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላም በማስጠበቅ በዓላማቸው ጸንተው መማራቸው ያስመሰግናቸዋል። ''ዛሬ የተመረቃችሁ ትምህርት በዚህ አበቃ ማለት አይደለም፤ ገና መጀመሪያችሁ ነው በስራ ላይ ትማራላችሁ፣ ከማህበረሰቡ ትማራላችሁ፣ ከሚገጥማችሁ ችግሮችና ከኑሮ ትማራላችሁ'' ያሉት ደግሞ የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ናቸው። ተመራቂዎች ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ብዙ መንገድ መኖሩን በመገንዘብ መጓዝ እንደሚኖርባቸው በመግለጽ ምክራቸውን ለግሰዋል። ''ሥራ ወደ እንናንተ አይመጣም'' ያሉት ኢንጂነር እንዳወቅ በውስጣቸው ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ለአገርና ለወገን በመስራት አገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ተማሪዎች በሚሰማሩበት አካባቢ ለሠላም፣ ለፍቅርና ለይቅርታ በመዘጋጀት ለአገር ሠላም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡም የአደራ መልዕክት አስተላፈዋል። በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ፣ ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ከተሸላሚዎቹ መካከል አንዷ የሆነችው አካል ጉዳተኛዋ ብርቅነሽ ፈካንሳ፤ ''አካል ጉዳኛ መሆን ውጤታማ ከመሆን አያግድም'' በማለት ተናግራለች። ''ማንኛውም ሰው ጥረት ካደረገ ለስኬት መብቃት ይችላል'' የሚል መልዕክት አስተላፋለች። ዩኒቨርሲቲው ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በቀጣዩ ዓመት በጤና ዘርፍ ሁለት መርሃ ግብሮችን እንደሚከፍት ለማዋቅ ተችሏል።