የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቃል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቃል
ሰኔ 29/2011 በበርካታ ውዝግቦች እየታጀበ ሲጓዝ የመጣው 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ፋሲል ከነማ፣ መቐለ ሰብእ እንደርታ ሲዳማ ቡና እድል ይዘው ግጥሚያቸውን ያደርጋሉ በዚህም ከውድድር ዘመኑ የመጨረሻው ሳምንት ጨዋታዎች መካከል ሁለቱ ቀደም ብለው አራት ሰዓት ላይ የሚደረጉ ይሆናሉ። ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ በተመሳሳይ 9:00 ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ለመሆኑ የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ለፋሲል ከነማ፣ መቐለ ሰብአ እንደርታ ወይስ ሲዳማ ቡና? ከእለቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሚታወቅ ይሆናል። እነዚህ ክለቦች የፊታችን እሁድ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ተጠብቋል። ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ በእኩል 56 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበላልጠው የዋንጫው ባለቤት ለመሆን የነገው 90 ደቂቃ ውጤት የሚወስናቸው ይሆናሉ። ከፌዴሬሽኑ ምላሽ እስከሚያገኝ ከሊጉ እራሱን ማግለሉን ያስታወቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ ጋር 4:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም እንዲጫወት የወጣው መርሃ-ግብር የሚያሳይ ቢሆንም ክለቡ በአቋሙ ከፀና ጨዋታው የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው። ከሊጉ መውረዳቸውን ካረጋገጡት ደቡብ ፖሊስ፣ መከላከያና ደደቢት ውጪ ሌሎቹ ክለቦች የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች መርሐ ግብሩን ለማሟላት የሚከናወኑ ናቸው። በመርሃ-ግብሩ መሰረት ሀዋሳ ከተማ ከደደቢት ነገ ነገ በ4:00 ሰዓት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ፣ አዳማ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ጅማ አባጅፋር ከደቡብ ፖሊስ በተመሳሳይ 9:00 ሰዓት ይገናኛሉ። የዋንጫ ተፋላሚዎቹ ክለቦች ደግሞ መቐለ ሰብአ እንደርታ በሜዳው ድራዳዋ ከተማን ሲያስተናግድ ፋሲል ከነማ ደግሞ ከሚዳው ውጪ ስሁል ሽረን የሚያገኝ ይሆናል። የኮከብ ግብ አግቢነቱን የመቐለ ሰብአ እንደርታው የፊት ተጫዋች አማኑኤል ገብረሚካኤል በ17 ጎሎች ሲመራ፣ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይና የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም በ16 እና በ15 ጎሎች ይከተላሉ።