የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

104
መቀሌ ሰኔ 2/2010 ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት በወቅታዊ ክልላዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ ማምሻውን ባስተላለፈው መግለጫ እንዳመለከተው ነገ በሚያካሒደው ስብሰባ የክልሉን ብሎም የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በዝርዝር ገምግሞ የሚወስደውን አቋም ለህዝብ ይፋ ያደርጋል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ጉዳይ ያሳለፈው ውሳኔ የሃገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ህወሃት ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም