ቀጥታ፡

ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትየጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

ሰኔ 25/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶክተር ዳንኤል በቀለን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾመ። ዶክተር ዳንኤል ያላቸው የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ኮሚሽኑን ለመምራት ብቁ ያደርጋቸዋልም ተብሏል። ተሿሚው ከኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነርነት በተጨማሪ ባላቸው ሙያ ሌሎች ስራዎችን በመስራት አገራቸውን እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ አባላት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግና በሙሉ ጊዜ መሰራት ያለበት በመሆኑ ይህ ጥያቄ ተገቢ አይደለም ተብሏል። ኮሚሽነሩ ስራቸውን ገና ሳይጀምሩ ይህ አይነት ጥያቄ ተገቢ አለመሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላቱ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቷ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል። በመሆኑም ተሿሚው  ከዋናው ተግባራቸው ተጨማሪ ስራዎችን ለመስራት  ለምክር ቤቱ አባላት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም። ምክር ቤቱ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምጽ ዶክተር ዳንኤል በቀለን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል። ኮሚሽነሩም በምክር ቤቱ ተገኝተው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም