የኢትዮጵያ ዳያሰፖራ ትረስት ፈንድ በአሜሪካ እየተካሄደ ባለው የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ጎን ለጎን የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዳያሰፖራ ትረስት ፈንድ በአሜሪካ እየተካሄደ ባለው የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ጎን ለጎን የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል
አዲስ አበባ ሰኔ 23/2011 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሰሜን አሜሪካ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያዊያን የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ አየተሳተፈ ሲሆን ከዝግጅቱ ተሳታፊዎችና ደጋፊዎች ጋር ለመመካከር የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ለ36ኛ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያዊያን የባህልና ስፖርት ዓመታዊ ፌስቲቫል ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በሰሜን አሜሪካ ጆርጅያ ግዛት አትላንታ ከተማ ተጀምሯል።
በዝግጅቱም የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የራሱ ስራዎች የሚያሳይበት ስፍራ ያለው ሲሆን የድርጅቱ ምክር ቤት አባላት፣ ሰራተኞችና ደጋፊዎች በተገኙበት በቀጣይ የድርጅቱን ተልዕኮ ለማሳካትበሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል። ትረስት ፈንዱ በርካታኢትዮጵያዊያንን በሚያሰባስበውና በአትላንታ በሌክውድ ስታዲዮም በሚደረገው ፌስቲቫል ከሚኖረው ዕለታዊ መደበኛ መርሃ ግብሮች በተጨማሪ የራሱ የሆኑ ልዩ ዝግጅቶች እንዳሉት አስታውቋል። ከእነዚህም መካከል ህዝባዊ መድረክ፣ ለትረስት ፈንዱ አስተባባሪዎች፣ ደጋፊዎችና ለደጋፊ አካላት የዕውቅና ሽልማቶች፣ የበጎ ፈቃድ አስተባባሪዎች ምልመላ፣ ለነባርና ለአዳዲስ ለጋሾች የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደቶችን ማስተዋወቅና ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት የሚሉት ይገኙበታል። 'አንድ ዶላር በአንድ ቀን ለተሻለች ኢትዮጵያ' በሚል መርህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጣር ከጥቅምት ወር 2018 ጀምሮ በ77 አገሮች ከሚገኙ 21 ሺህ ድጋፍ አድራጊዎች በተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶች 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አሰባስቧል። በአዲስ አበባ የተቋቋመው የድርጅቱ ጽህፈት ቤትም በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ቁልፍ ችግሮችን በጥናት ለይቶ የፕሮጀክት ትልመ ሀሳብ ለትረስት ፈንዱ ቦርድ እንዲጸድቅ አቅርቧል። የመንግስታቱ የልማት ፕሮግራም አዲስ አበባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ ቢሮ ለሁለት ዓመት ድጋፍ እንዳደረገለት ድርጅቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። ከፖለቲካ አጀንዳና ከማንኛውም ወገንተኝነት ገለልተኛ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፤ በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ በማሰባሰብ ለማህበረ ምጣኔ ሐብታዊ አገራዊ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ማድረግ ዓላማው መሆኑን አመልክቷል።