ፕሬዚደንት ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ጋር በንግድ ጦርነት ዙሪያ `ፍሬያማ` ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተዋል

85
ሰኔ 21/2011የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚደንት ዢ ዚፒንግ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥላ እያጠላ ያለውን የንግድ ጦርነት ለማርገብ ፍሬያማ የሆነ ውይይት እንደሚያደርጉ ተሰፋ  ተጥሏል ሲል ሬውተርስ  ዘግቧል። የንግድ አለመግባባት እና የአለም አቀፍ ንግድ  ፍጥነት መቀነስ በጃፓን ኦሳካ ከተማ ለሁለት ቀን እየተካሄደ ባለው የቡድን 20 አባል ሀገራት  ስብሰባ ላይ ችግሩ እንደሚፈታ በመረጃው ሰፍሯል። ትራምፕ እና ዢ በእርፍት ስዓታቸው ተገናኝተው ያወሩ ሲሆን ቅዳሜ ዕለት የአንድ ለአንድ ንግግር ለማድረግ እንደተዘጋጁ በመረጃው ተገልጿል። የቻይና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዩ ከትራምፕ የንግድ  ፀሐፊ ስቲቨን ሙቺን እና የንግድ ተወካዩ ሮበርት ላይትዘር ጋር የአሜሪካ ተወካዮች በሚገኙት ሆቴል ተገናኝተው መወያየታቸውን የቅርብ ምንጭ ለሬውተርስ ገልጿል። በአለም ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት ሁለቱ ሀገራት ከገቡበት የንግድ ጦርነት ለመውጣት በቡድን 20 ስብሰባ ላይ ጎን ለጎን በሚያደርጉት ንግግር ውጥረቱ ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመደገፍ የሁለትዮሽ የንግድ ውይይት ባደረጉበት ወቅት  ምን እንደሚከሰት እና ምን እንደሚፈጠር እናያለን ቢያንስ ውይይቱ  ውጤታማ ይሆናል  በማለት  ትራምፕ ለሬውተርሱ ዘጋቢ ተናግረዋል። ትራምፕ ከቻይና  በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የ250 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታሪፍ መጣላቸው እና በዚህም የንግዱ እንቅስቃሴ መቀዛቀዙን በማስተዋስ ይህ የታሪፍ ማዕቀብ ወደ 300 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያሻቅብም በመረጃው ለትውስታ ቀርቧል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም