ቀጥታ፡

ምርት ገበያው ሽምብራን ወደ ዘመናዊ ግብይት አስገባ

አዲስ አባባ ሰኔ 21/2010 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሽምብራ ምርትን ወደ ዘመናዊ የግብይት ስርዓት ማስገባቱን አስታውቀ። ሽምብራን ወደ ዘመናዊ የምርት ገበያ ሥርዓት ማስገባት ፤ በዘርፉ ምርት የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ፣ አቅራቢዎችን እና ላኪዎችን ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ የአገሪቱንም ምጣኔ ኃብት ያግዛል ተብሏል። የኢትዮጵያ ምርት ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ እንድገለጹት፤ ምርት ገበያው የሽምብራ ምርትን ከሰኔ 21 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በአምስት ቅርንጫቹ መቀበል መጀመሩን አስታውቀዋል። የሽንብራ ምርት በውጭ ገበያ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት አቶ ወንድማገኘሁ ምርቱ ወደዘመናዊ ንግድ ስርዓት በማስገባት ከዘርፉ ይበልጥ መጠቀም እንደሚቻል አስረድተዋል። የሽምብራ ምርት በዘመናዊ የግብይት ሥርዓት በኩል መፈጸሙ በውጭና በአገር ውስጥ ግብይት አስተማማኝ አቅርቦት እንዲኖርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለመገበያየት እንደሚያስችልም ገልፀዋል። በተጨማሪም አቅራቢዎችም  ግብይት  በተፈጸመ  ማግስት  የምርታቸውን ዋጋ እዲያገኙ እንደሚያስችልም አክለዋል። ምርት ገበያው ካሉት 23 ቅርንጫች በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቡሬ፣ ኮሞቦልቻ እና ጎንደር ባሉ የምርት መቀበያ ጣቢያዎች ለመቀበል በቂ ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል። በተያዘው በጀት ዓመት  የአኩሪ አተርና  ሽምብራ  ምርትን ወደ ግብይት  በማስገባት  ሰባት የነበሩትን  የግብይት ምርቶች  ወደ ዘጠኝ ማድረስ መቻሉን አመላክተዋል። በቅርቡ ወደ ግብይት ሥርዓቱ ከገባው አኩሪ አተር እሰከ ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓም  ድረስ 1 ነጥብ 22 ቢሊየን  ብር የሚደርስ  ግብይት መከናወኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው ተናግረዋል። በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቡና በማምረትና በመገበያየት ላይ ለተሰማሩ ሴቶች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት በዛሬው እለት አስመርቋል።                    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም