ቀጥታ፡

ሰላማቸውን የሚያደፈርሱ ኃይሎችን እንደሚቃወሙ የጊምቢ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

ሰኔ18/2011 የአካባቢያቸውን ሰላም ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችን ድርጊት በጽኑ እንደሚያወግዙ የምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች በተቃውሞ ሰልፍ ገለጹ። ነዋሪዎቹ ዛሬ በጊምቢ ከተማ ባካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ በጫካ የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች የኦሮሞን ህዝብ እንደማይወክሉ ገልጸዋል። ከሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል በከተማው ቀበሌ 01 የሚኖሩት አቶ መዝገቡ በንቲ እንዳሉትመንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉአመቺ ሁኔታዎችን ቢያመቻችም ራሱን “አባዎሸኔ” ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል የህዝቡን ሰላምእየነሳ ነው። ይህ ኃይል አመራሮችን በማገት ከማስፈራራትና ከመግደል ባለፈ ህዝቡን እያሰቃየ በመሆኑ ድርጊቱን ለመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዞኑ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ኃይል የኦሮሞን ህዝብ የማይወክል በመሆኑ እንደሚቃወሙትየገለጹት አቶ መዝገቡ፣ መንግስት በዞኑ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረትእንዲያጠናክር ጠይቀዋል። “የሸኔን ድርጊት ለማክሸፍ ከመንግስት ጎን ለመቆም ዝግጁ ነኝ” ብለዋል። በከተማው የቀበሌ 02 ነዋሪ አቶ አሰፋ በየነ በበኩላቸው የዞኑ የፀጥታ ሁኔታ በአስቸጋሪ ሁኔታውስጥ በመሆኑ አርሶ አደሩ የእርሻ ስራውን በወቅቱ ማረስ እንዳልቻለ አመልክተዋል። በንግድ ሥራ የተሰማሩትም ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን ካለመቻላቸው በላይ ሰው በሰላም ወጥቶ ለመግባት እየተቸገረ መሆኑን ነው የገለጹት። “በዞኑ ጫካ ውስጥ ሆነው ህዝቡን እያሸበሩ የሚገኙ የአባዎሸኔ ኃይሎች ማንንም የማይወክሉበመሆናቸው አጥብቀን እንቃወማለን” ብለዋል። በከተማው ቀበሌ 01 የሚኖሩት አቶ ታምራት ጉተታ በበኩላቸው “ሸኔ” ተብሎ በሚጠራው ታጣቂኃይል የአካባቢያቸው ሰላም ባለመረጋጋቱ ሰው ወጥቶ መግባት እንዳልቻለ ተናግረዋል። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ታግተው እርምጃ የሚወሰድበት አጋጣሚ መኖሩን ጠቁመውበእዚህም አመራሩ በየቦታው ተዘዋውሮ የመንግስት ሥራን ለመስራት እየተቸገረ መሆኑን አቶታምራት ገልጸዋል። “ታጣቂ ኃይሎቹ ማንንም ስለማይወክሉ ህዝቡ አንድነቱን አጠናክሮ ሊያወግዛቸው” ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአዲስ አበባ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እንደሚቃወሙና ድርጊቱ በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ በመሆኑ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ተናግረዋል። የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ትግስቱ በበኩላቸውየምዕራብ ወለጋ ዞን ህዝብ ግድያ፣ አፈናና እንግልት የሚያደርሱበትን አካላት በመቃወም አደባባይመውጣቱንና በቀጣይ በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችም ተመሳሳይ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተናግረዋል። መንግስት ያሰፋውን የዴሞክራሲ ምህዳር በመጠቀም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድመታገል እየቻሉ የመንግስተን ጥሪ ባለመቀበል መሳሪያ ይዞ ጫካ በመግባት ህብረተሰቡ ላይ ኢሰባዊ ድርጊት መፈጸም የሚወገዝ ተግባር መሆኑንም አስታውቀዋል። ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ ከሚል አካል የማይጠበቅ በመሆኑም ህዝቡ በእዚህ አካል እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት እጥብቆ እየተቃወመ መሆኑንም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም