ቀጥታ፡

በኦሮሞ ህዝብ ስም ታጥቆ ጫካ የሚገኘው ኃይል አይወክለንም…የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች

ሰኔ18/2011በኦሮሞ ህዝብ ስም ታጥቆ ጫካ የሚገኘው ኃይል የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም በማለት የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች ዛሬ ባካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ አስታወቁ። በዞኑ የበደሌ ገቺ ደዴሳና ጮራ ወረዳዎችና የበደሌ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ባካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍበኦሮሞ ህዝብ ስም ታጥቆ ጫካ የሚገኘው ኃይል እንደማይወክላቸው ተናግረዋል። ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከልም "በኦሮሞ ህዝብ ስም ታጥቆ ጫካ የሚገኘው ኃይልአይወክለንም"፣"በኦነግ ስም በመታጠቅ ሰላምን ማወክና ህዝቡን ማሸበርን እንቃወማለን" የሚሉናየመሳሰሉት ይገኙበታል። ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በመሰባሰብ በበደሌ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ተቃውሟቸውንያሰሙት ሰልፈኞቹ ሰሞኑን በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና በመከላከያ ጀነራሎች ላይየተፈጸመውን ግድያም አውግዘዋል። መንግስት የዚህን ሴራ አስተባባሪዎች ተከታትሎ ለህግ እንዲያቀርብም ጠይቀዋል። ከሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል የበደሌ ከተማ ነዋሪው ወጣት ጀማል አብዱ እንዳለውበአሁኑ ወቅትሀገሪቱን ወደ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ሁሉም ዜጎች ተግባብተው      በጋራ እየሰሩ ባሉበት ሁኔታ የትጥቅትግል ቦታ የለውም።  ኦነግም ከመንግስት ጋር እርቅ ፈጥሮ ወደ ሰላማዊ ትግል የገባ በመሆኑ በኦነግ ስም ታጥቆ ጫካየሚገኘው ሽፍታ እውቅና እንደሌለው ተናግሯል። በሰልፉ ላይ የተገኙት የቡኖ በደሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሻፊ ሁሴን እንዳሉት መንግስት የዜጎችንደህንነት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር በመሆን የህግ ማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።  ህብረተሰቡም የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ በመጠበቅ በልማቱና በለውጡ ቀጣይነት ላይ የጀመረውንአስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም