የጄኔራል ሰዓረ መኮንን አስከሬን ሽኝት ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን አስከሬን ሽኝት ተደረገለት
ሰኔ 18/2011የጀነራል ሰዓረ መኮንን አስከሬን ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ደማቅ ስነ-ስርዓት ዛሬ ሽኝት ተደርጎለታል። የጀነራል ሰዓረ መኮንን አስከሬን ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ደማቅ ስነ-ስርዓት ዛሬ ሽኝት ተደርጎለታል። በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተከናወነው ሽኝት የተነበበው የጄኔራሉየህይወት ታሪክእንደሚያመለክተው ጀነራሉ ከትጥቅ ትግሉ ጊዜ ጀምሮ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜአገራቸውንና ህዝባቸውን አገልግለዋል። ከአባታቸው ከአለቃ መኮንን ይመርና ከእናታቸው ወይዘሮ ህይወት ይህደጉ በትግራይ ክልል ስሜንምዕራብ ዞን በአስገደ ፅንብላ ወራዳ እንዳባጉና ከተማ በ1954 ዓ.ም የተወለዱት ጀነራል ሰዓረበትጥቅ ትግል ወቅትም ሆነ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ የተሰጧቸውንግዳጆች በብቃት የተወጡ ብርቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነበሩ። በወጣትነት እድሜያቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማቋረጥ በ1969 ዓም ወደ ትጥቅትግል የተቀላቀሉት ጀነራል ሰዓረ በአገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ምክትል ጠቅላይ የኢታማዦርሹምነትን ጨምሮ በተለያየ ከፍተኛ ኃላፊነት አገራቸውን በታማኝነት አገልግለዋል። በተለይም የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ሰራዊቱ በወታደራዊሳይንስና ጥበብ የተካነ እንዲሆን የሚያስችል የትምህርትና ስልጠና ተቋማት በመገንባት ትልቅ ሚናየተጫወቱ የጦር መኮንን እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው አመልክቷል። በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ የተፈጠረውን የዜጎች መፈናቀልለመከላከል ሰራዊቱ በሚፈቅድለት የአሰራር አግባብ መሰረት ግዳጁን እንዲወጣ በማድረግ ህዝቡበሰላም ወጥቶ እንዲገባ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። የአንድ ወንድና የአንድ ሴት ልጆች አባት የነበሩት ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ህይወታቸው እስካለፈበትሰኔ 15 ቀን 2011 ዓም ድረስ የአገር መከላከያ ጠቅላይ የኢታማዦር ሹም በመሆን አገራቸውንእያገለገሉ ነበር። ጀነራል ሰዓረ ህይወታቸው ያለፈው ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከተሞከረው የመንፈቀለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ በተፈጸመባቸው ጥቃት ነው። በጥቃቱ በጠቅላላው የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪያቸው እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምግባሩ ከበደ ይገኙበታል። በአዲስ አበባም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ በጠባቂያቸው በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል። የጀነራል ሰዓረ መኮንን ቀብር ስነ-ስርዓት ነገ በመቀሌ ይካሄዳል ተብሏል። በሚሊኒየሙ ስነ-ስርዓት ላይ ከጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጋር ህይወታቸው ያለፈው ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራም አስክሬን ወደመቀሌ ተሸኝቷል።