ወጣቶች እውቀትና ጉልበታቸውን ለአገር ግንባታ እንዲያወሉ ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
ወጣቶች እውቀትና ጉልበታቸውን ለአገር ግንባታ እንዲያወሉ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ ሰኔ 15/2011 "የተጀመረውን ለውጥ በስኬት ለማስቀጠል ወጣቶች እውቀትና ጉልበታቸውን ለአገር ግንባታ ማዋል ይገባቸዋል" ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። "የወጣቶችን ጉልበት፣ ችሎታና እውቀት ለፈጣን ልማትና አስተማማኝ ሰላም" በሚል መሪ ሐሳብ በአዳማ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 12ተኛው የኦሮሚያ ወጣቶች ኮፍረንስ ተጠናቋል። ከክልሉ ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣቶች በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ማጠናቀቂያ ላይ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በወጣቶቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በፖለቲካው መስክ የተገኘውን ድል በኢኮኖሚውም መድገም አስፈላጊ መሆኑን በኮንፈረንሱ ላይ አጽንኦት ከተሰጣቸው ነጥቦች መካከል ተጠቃሽ ነው። በተለይም ለውጡን ለማስቀጠል ወጣቶች ከስሜታዊነት በመውጣት የስራ ባህላቸውን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን ተወያዮቹ አንስተዋል። ወጣቶች የኦሮሞ ባህል መገለጫ ከሆኑት መልካም እሴቶች መካከል መደማመጥን፣ መቻቻልንና መከባበርን ተግባራዊ በማድረግ በምክንያታዊነት መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸውም ነው የተጠቆመው።
ወጣቶቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው፣ ምቹ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸውና የብድር አቅርቦት እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል። በከተሞች የህግ የበላይነት እንዲከበርና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮች ፈጣን መፍትሄ እንዲፈለግላቸውም አመልክተዋል። ምክትል ፕሬዝዳንት ሽመልስ በሰጡት ምላሽም፤ ወጣቶቹ ያነሷቸው ችግሮች በተጨባጭ መኖራቸውን ጠቁመው፤ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች የሚፈቱት በትብብርና በአንድነት በሂደት መሆናቸውን አስረድተዋል። በመሰረተ ልማት ዝርጋታ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ በኢንቨስትመንትም ህገ ወጦችን አጣርቶ እርምጃ መውሰዱ እና ህጋዊነትን ለማበረታታት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ሰላምና ጸጥታ በማስከበሩ ላይም ሰፊ ትግስት ያሳየው መንግስት አሁን አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ሰላምና ጸጥታ እንደሚያስከብር አብራርተዋል። ለዚህም አባቶች አውርሰው ያለፉትን የገዳ ስርዓት እሴቶች መሰረት በማድረግ በፍቅር፣ በአንድነትና በስራ ልቆ የመገኘት ጀግንነትን ማሳየትና በተግባር ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጠውታል። ለዚህም ወጣቱ የስራ ባህሪውን በመለወጥና በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚጠበቅበት አብራርተዋል። በአገሪቷ ብሎም በኦሮሚያ ክልልበፖለቲካ መስክ የመጣውን ለውጥ በመጠቀም በኢኮኖሚው መስክ እመርታዊ ለውጥ እንዲመዘገብ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። "የፖለቲካ ስልጣን ለኢኮኖሚው ለውጥ መሳሪያ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ወጣቱ መስዋዕት ከፍሎ ለመላው አገሪቷ ያጎናጸፈው ነጻነት ከግብ የሚደርሰው ግዴታውን በስራ ተወጥቶ ህዝብን ከአስከፊ ድህነት ማላቀቅ ሲችል መሆኑን ተናግረዋል። በመሰረተ ልማት እጦት፣ አየር መዛባትና በበረሃማነት መስፋፋት አስከፊ ህይወት እየመራ ያለውን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።