ትራምፕ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ገለፁ - ኢዜአ አማርኛ
ትራምፕ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ገለፁ
ሰኔ 15/2011የአሜሪካው ፐሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንዳማይፈልጉ የገለፁ ሲሆን ግጭት ከተከሰተ ግን አውዳሚ ወደ ሆነ ሁኔታ እንደሚያመራ አስጠንቅቀዋል፡፡ “ወደ ጦርነት መግባት አልፈልግም፣ነገር ግን ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አውዳሚ ይሆናል ይህ እንዲሆን ግን ፍላጎት የለኝም” ብለዋል ለኤን ቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ፣ ትራምፕ ኢራን መታ ለጣለችው ድሮን የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ የታሰበውን መሰረዛቸውንም ሲጂቲን በመረጃው አስፍሯል፡፡
እንደ ዘገባው የኢራን ከመሬት ወደ አየር የተወነጨፈ ሚሳኤል የአሜሪካን አለም አቀፍ የቅኝት ሰው አልባ አውሮፕላን መቶ መጣሉ የሚታወስ ሲሆን ኢራን “የአየር ክልሌን በመጣሱ መትቸዋለሁ “ ስትል አሜሪካን በበኩሏ የአየር ክልሉ አለም አቀፍ የአየር መተላለፊያ ነው ብላለች፡፡ ትራምፕ በቲውተር ገፃቸው ደጋግመው እንደገለፁት ኢራን ላይ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድና ኢራን የኒኩለር ማበልፀግና የሚሳኤል ፕሮግራሟን እንድታቋርጥ የተጣለው የኢኮኖሚ ማእቀብን ለማንሳት እንደማይቻኮሉ መግለፃቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡