ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው 750 ሚሊዮን ዶላር ያገኘችው 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው-ሚኒስቴሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው 750 ሚሊዮን ዶላር ያገኘችው 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው-ሚኒስቴሩ
ሀዋሳ ሰኔ 14ቀ/2011 ኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው 750 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡: ባለፉት ሶስት ዓመታት ከማዕድን ዘርፍ የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ዶላር እየቀነሰ መጥቷል:: በሚኒስቴሩ የሀብት ማፈላለግና ዓለም አቀፍ ትብብር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገረመው ነጋሣ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ የተገኘው ገቢ ከታቀደው ያነሰ ሆኗል። ገቢው ከዕቅዱ ያነሰው ከፍተኛ የማዕድን አቅርቦት ድርሻ ባላቸው ክልሎች ላይ በተፈጠረ የፀጥታና የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት መሆኑንም አመልክተዋል ፡፡ የፀጥታው ችግር ከገቢው ከ60 እስከ 70 በሚያመነጩት ክልሎች የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት የተናገሩት አቶ ገረመው፣ይህም ለውጭ ንግድ በሚቀርበው ማዕድን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ብለዋል። በተለይ ማዕድናት ከሌሎች ምርቶች ይልቅ በቀላሉ ስለሚጓጓዙ የኮንትሮባንድ ንግድ ምቹነት እንዳላቸው አስረድተዋል ፡፡ በግዙፍ የማዕድን ኩባንያዎች ደረጃ የለገደምቢ ወርቅ ኩባንያ በአካባቢ ብክለትና ጤና ችግር ምክንያት ከምርት መታገድ ገቢው እንዲቀንስ እንዳደረገው ገልጸዋል ፡፡ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆንና ለአሰራር የተመቸ የግብይት ዓዋጅና ደንብ አለመኖርም ገቢው እንዲቀንስ ማድረጉን ኃላፊው አስረድተዋል ፡፡ የግብይት ሥርዓቱን የሚያቀላጥፍና ክልሎችንም ባለድርሻ የሚያደርግ የማዕድን ግብይት ዓዋጅና ደንብ መጽደቁን የተናገሩት አቶ ገረመው፣ ዘርፉ የሚመራበት ረቂቅ የማዕድን ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለመጽደቅ በሂደት ላይ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡ አምራቹ ማህበረሰብ ባለበት ምርቱን ለመረከብ የሚያስችሉ ስልቶችን ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ የለገደምቢ ወርቅ ኩባንያን በተመለከተም ሚኒስቴሩንና የሚመለከታቸው አካላትን ያሳተፈ ጥናት ተካሂዶ ለውሳኔ መቅረቡንም አመልክተዋል ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ማዕድን ልማት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ይርዳው ነጋሽ ከክልሉ በተለይ በቦረና በኩል በኮንትሮባንድ የሚንቀሳቀሰውን ማዕድን ለመቆጣጠር የፀረ-ኮንትሮባንድ ግብረ-ኃይል መቋቋሙን አስታውቀዋል ፡፡ ለአብነትም በቅርቡ ስምንት ኪሎ ግራም ወርቅ በሞያሌ በኩል ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል በኅብረተሰቡና በግብረ-ኃይሉ ትብብር መያዙን ተናግረዋል፡፡ የለገደምቢ ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያን አስመልክቶም ገለልተኛ በሆነ መንገድ ጥናት መካሄዱንና የጥናቱ ውጤት የሚያመላክታቸው የመፍትሔ ሀሳቦች ውሳኔ ሲሰጥባቸው ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል ፡፡ የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ክልሉ ባለፉት ዓመታት ከ400 እስከ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ያቀርብ እንደነበር አስታውሰው፣ ባለፉት 11 ወራት ያቀረበው 220 ኪሎ ግራም እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በክልሉህጋዊየማዘዋወርፈቃድያላቸውነገርግንለብሔራዊባንክከማቅረብይልቅበሕገ-ወጥመንገድየሚንቀሳቅሱእየተበራከቱመምጣታቸውንናባለፉትወራትከ20 በላይየሚሆኑትፈቃዳቸውመሰረዙንተናግረዋል፡፡ የማዕድንናነዳጅሚኒስቴርየ2011በጀትዓመትየ11 ወራትአፈፃፀምናየ2012 በጀትዓመትዕቅድእንዲሁምእየተዘጋጀባለውየ10 ዓመታትመሪዕቅድላይከዘርፉባለድርሻአካላትጋርበሀዋሳከተማእየመከረነው።