ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነታቸውን ማጠናከር አለባቸው-የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2011 የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነታቸውን በማጠናከር ፍትህና ነፃነታቸውን እንዲያስከብሩ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት  ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለውጡን ለማስቀጠል ከመንግስት እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አስተላልፏል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ሰይድ ይመር እንደሚሉት ለውጡን ለመቀልበስና ህዝቦችን በማጋጨት የራሳቸውን ጥቅም ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ላይ መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያሰከብር አሳስበዋል። አቶ ሰይድ አክለውም በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በተለይም በባለ ሃብቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት ለሃገሪቱ ልማት እንቅፋት እንደሚሆን ተናግረው መንግስት ክትትል እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የመከላከያ ሰራዊቱም ከሃገሪቱ የተሰጠውን ሃላፊነት የዜጎችን ሰላምና የአገሪቷን ደህንነት በመጠበቁ ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአሁን ጊዜ የአባላቱ ቁጥር 196 ሺህ መድረሱን በዚሁ ጊዜ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም