የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለ2020 ምርጫ ቅስቀሳ ጀመሩ

72

ሰኔ 12/2011 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2020 ምርጫ በድጋሚ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለመመረጥ  ቅስቀሳ በይፋ በጀመሩበት ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ይፋዊ ንግግር አድርገዋል።

የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካዩ “ሁለተኛዋ ቤቴ” በሚሏት ፍሎሪዳ ግዛት ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ”የአብሮነት ጉዟችን ይቀጥላል”  ሲሉ ተናግረዋል።

80 ደቂቃ ያህል በወሰደው ንግግራቸው በ2016 የተጠቀሟቸውን የምርጫ ቅስቀሳ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የዴሞክራት ፓርቲን የወቀሱት ፕሬዚዳንቱ፤ “ሀገራችሁን ለመበታተን እየሞከሩ ነው” ብለዋል።

 “የአሜሪካን የታላቅነት ጉዞ ዳግም እናስቀጥላለን”  ሲሉም ለደጋፊዎቻቸው ገልጸዋል።

ወደ አሜሪካ የሚደረግ ህገወጥ ስደትን በማስቆም ስራቸውን በትኩረት እንደሚቀጥሉ ነው የጠቀሱት።

“ሀገራችን ለህግ ተገዥ የሆኑ ዜጎቿ መኖሪያ እንጂ የህገወጦች መመሸጊያ እንደማትሆን እናስባለን” ብለዋል።

በስደተኝነት ጉዳይ ላይ ከረር ያለ አቋም የያዙት ፕሬዚዳንቱ ዴሞክራቶች ህገወጥ ስደትን ህጋዊ ለማድረግ የሚሞክሩ፣ ሀገራችንን ለማውደም የሚሰሩ “አክራሪ የግራ ዘመም መንጋዎች” ናቸው ሲሉ በጠንካራ ቃል ተችተዋቸዋል።

“በ2020 በሚደረግ ምርጫ ለዴሞክራቶች የሚሰጥ ድምፅ አክራሪ “በአሜሪካ ሶሻሊዝም እንዲያቆጠቁጥ እና የሀገሪቱ ህልም እንዲመክን የሚያደርግ ነው ሲሉም” ተናግረዋል።

ፍሎሪዳ ግዛት የዴሞክራትና የሪፐብሊካን ፓርቲዎች ከፍተኛ የፉክክር ግዛት ስትሆን፤ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2016 በተካሄደው ምርጫ በጠባብ ልዩነት ማሸነፋቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም