የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
ሰኔ 10/2011 የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኦቢያንግ ለስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ቦሌ አየር ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዝዳንቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እና በወቅታዊ ጉደዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። ኢትዮጵያና ኢኳቶሪያል ጊኒ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል ዕድሜ ያለውና ዘርፈ ብዙ የጋራ ስምምነቶች የተፈረሙበት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው። አገሪቷ በአዲስ አበባ ኤማባሲ ያላት ሲሆን በአንጻሩ ኢትዮጵያ በኢኳቶሪያል ጊኒ ኤምባሲም ሆነ የቆንፅላ ጽሕፈት ቤት የላትም።