ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ደም ለገሱ

67
ሰኔ 10/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደም የለገሱት በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም ዓቀፍ የደም ልገሳ ቀንን በማስመልከት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓለም አቀፍ የደም ልገሳ ቀንን ምክንያት በማድርግ የደም ልገሳ አደረጉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኅብረተሰቡ ይህንን በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የነፍስ አድን ስጦታ ለማበርከት እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘነው መረጃ ያመላክታል። ዓለም አቀፉ የደም ልገሳ ቀን በኢትዮጵያ የሚከበረው ዘንድሮ ለ16ኛጊዜ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም የደም ልገሳ ማድረጋቸውም  ይታወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም