ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፅዳትና የችግኝ ተከላ አካሄዱ

104
አዲስ አበባ ሰኔ/9 2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብር አህመድ ዛሬ ማለዳ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተው የፅዳትና የችግኝ ተከላ ስራ አከናውነዋል። በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ በተካሄደው ፅዳትና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ፣ የህክምና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞችም ተሳትፈዋል። በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉትም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አርአያነት መላውን ህዝብ ለስራ የሚያነሳሳ ነው። ህዝቡም የእርሳቸውን አርአያ በመከተል ከሰፈር እስከ አደባባይ በመውጣት በፅዳትና በችግኝ ተከላው ስራ መሳተፍ እንዳለበት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የፅዳት ስራ ማከናወን ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የችግኝ ተከላውንም እንዲሁ በተደጋጋሚ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም