የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ነገ ይወጣል

80
አዲስ አበባ ሰኔ 1//2010 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ ለኢዜአ ያደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው፤ የ1997 ዓ.ም ነባር ተመዝጋበው  ምዝገባቸውን በ2005 ያደሱና መቆጠብ ያለባቸውን ያህል ገንዘብ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች በዕጣው ይካተታሉ። የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ  በተገኙበት ዕጣቸው የሚወጣው የ20/80 ቤቶች ብዛት ከ2 ሺህ 500 በላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም