በቀጣዩ በጀት ዓመት ለእኩል ስራ እኩል የደሞዝ ክፍያ ሥርዓት ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል

100
ሰኔ 5/2011 በተመሳሳይ መስኮች ለተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች በቀጣዩ በጀት ዓመት አንድ ወጥ የደሞዝ ክፍያ ሥርዓት ሊጀመር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአገሪቷ በመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ አካፋፈል ላይ ወጥ የሆነ አሰራር እንደሌለና በእኩልና ተመሳሳይ ስራ ላይ ያሉ ሰራተኞች እኩል ክፍያ እንደሌላቸው ይታወቃል። መንግስት ይህንን ችግር ለመፍታት ከ2008 አንስቶ ለእኩል ስራ እኩል ክፈያ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናት  መጀመሩ ይታወሳል። ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንዳሉት ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በቀጣዩ በጀት ዓመት መጀመሪያ ተባራዊ ይሆናል ። ተግባራዊ የሚደረገውም በዝቅተኛ የደሞዝ እርከን ባላቸው ሰራተኞች ሲሆን በዚህም ሰራተኞቹ ተመሳሳይና የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል። የደሞዝ ክፍያ ሥርዓቱ ተግባራዊ የሚደረገው ደረጃ በደረጃ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የሆነው የአገሪቷ የገቢ መጠን እየታየ በሁሉም የደሞዝ እርከን ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም