ቀጥታ፡

የህዝብና ቤት ቆጠራ ለአንድ አመት ተራዘመ

አዲስ አበባ  ሰኔ 3/2011 አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባካሄዱት ልዩ የጋራ ስብሰባ ወሰኑ። 5ኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ የጋራ ስብስባ ዛሬ  ተካሂዷል። ምክር ቤቶቹ የአራተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሁለተኛ ጊዜ ለማራዘም በተሻሻለው የህገ-መንግስቱ  አንቀጽ 103 መሰረት የቀረበውን ውሳኔ ሃሳብ መርምረው በአብላጫ ድምጽ አስጽቀዋል። የምክር ቤቶቹ አባላት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው ቆጠራው እንዲራዘም  የወሰኑት። ውሳኔው የፀደቀው በ30 ተቃውሞ እና በ3 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው። በውይይቱ ላይ ቆጠራው ከአንድ አመት በላይ ላልተወሰነ ጊዜ ይራዘም የሚልና አሁን ላይ ያለው የሰላም  ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ ለ6 ወር ብቻ ይራዘም የሚል የመከራከሪያ ሃሳብ ቀርቦ  ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለአንድ ዓመት ይራዘም በሚለው ጸድቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም