ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከሱዳን እሥር ቤት የተፈቱ ኢትዮጵያውያንን ይዘው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

86
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሱዳን ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁ በእስር ላይ የነበሩ 78 ኢትዮጵያዊያንን ያስፈቱ ሲሆን 35ቱ ትናንት ምሽት አብረዋቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። የዶክተር አብይ የሱዳን ጉዞ የአልበሽር መንግስት ከወደቀ በኋላ የተፈጠረው አለመረጋጋት እንዲቆም ለማስማማት ሲሆን ቀደም ሲል 78 ኢትዮጵያዊያን እስረኞችን ለማስለቀቅ የተጀመረው ጥረት እልባት እንዲያገኝም አድርገዋል። ከእስረኞቹ መካከል 20 ዓመት ድረስ የተፈረደባቸው ይገኙበታል፤ ከተለቀቁት 78 ኢትዮጵያዊያን መካከል ግማሽ ያህሉም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አዲስ አበባ ገብተዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተመለሱት በካርቱም ታስረው የቆዩት ሲሆኑ በሱዳን የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የነበሩት ኢትዮጵያዊያን እስከ ቀጣዩ ሳምንት ወደ አገራቸው ይገባሉ። ኢዜአ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝቶ ያነጋገራቸው ዜጎች በእስር ይደርስባቸው ከነበረው እንግልት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥረት ተለቀው ለአገራቸው በመብቃታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ወደ አገራቸው የተመለሱት እስረኞች በሱዳን ማረሚያ ቤት የስራ መደራረብ፣ በቂ ምግብ አለማግኘትና ድብደባ ይደርስባቸው እንደነበርና ከአሁን በኋላ በአገራቸው ሰርተው ማደግ እንደሚፈልጉም አተናግረዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም