ቀጥታ፡

ተቋማቱ ለአገር ግንባታና ለአንድነት መጠናከር የሚጫወቱትን ሚና እንዲያሳድጉ ምክር ቤቱ አሳሰበ

ዓርባ ምንጭ ግንቦት 30 /2011  የዴሞክራሲ ተቋማት ለአገር ግንባታና ለአንድነት የሚጫወቱትን ሚና ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ ፡ አፈ-ጉባዔ ታገሰ በዓርባ ምንጭ ከተማ በተዘጋጀ የጋራ ምክክር መድረክ ላይ እንዳስገነዘቡት ተቋማቱ ለአገር ግንባታና ለአንድነት መጠናከር ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህም በኢኮኖሚ የዳበሩ አገሮች የተፈጠሩት ተቋማት የተጫወቱትን በአገሪቱ የሚገኙ ተቋማት ለሁለንተናዊ ዕድገት ሊያውሉት ይገባል ብለዋል። መንግሥት ተቋማቱ ተግባራቸውን በብቃት እንዲወጡ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ ለአብነትም ሕጎችን ማሻሻል፣ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በአገር ውስጥ ሰላማዊ ትግል የሚያደርጉበትን ሁኔታ መፍጠርን ጠቅሰዋል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ከመፈታታቸዉም በላይ፤ ፓርቲዎች የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ሥራ መግባታቸው መንግሥት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ያለውን ትኩረት እንደሚያመለክት አቶ ታገሰ ገልጸዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሴቶችና ህጻናት ኮሚሽነር ወይዘሮ መሠረት ማሞ በበኩላቸው ከግንዛቤና አመለካከት ክፍተቶች ጉድለት የመብት ጥሰቶች እንደሚታዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሥልጣን ባለቤት ሕዝብ ለመብቶቹ ተገቢዉን ጥበቃና አገልግሎት እንዲያገኝ ተቋማቱ ከምክር ቤቱ በጋራ በመገናኘት በችግሮች ዙሪያ መወያየታቸው አበረታች ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የፈደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነር አቶ አየለ ሙሉዓለም እንዳሉት ኮሚሽኑ ምክር ቤቱ ሕግ አውጪው አካል እንደመሆኑ ሥራቸውን ከመከታተልና ከመቆጣጠር አንጻር እንደሚሰራ መግለጹ ተቋሙ ሚናውን የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ያስችለዋል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። በመድረኩ የሕግ አውጪዉ ፣ ሕግ አስፈጻሚዉና ሕግ ተርጓሚዉ መካከል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ባለመዘርጋቱ በልማት ፣ በሰላምና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የገጠሙትን ችግሮች ለመፍታት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ተመልክቷል ፡፡ በተቋማቱላይየሚታዩችግሮችናመፍትሄዎችዙሪያየሚደረገዉውይይትነገምይቀጥላል። በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል ፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም