የነገሌ ከተማ ነዋሪዎች የሕግ የበላይነት እንዲከበር በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ

90
ነጌሌ ግንቦት 30 / 2011   በኦሮሚያ ክልል የነጌሌ ቦረና የሕግ የበላይነትን እንዲከበር የጠየቁበትን ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መንግሥት የዜጎችን የመዘዋወርና የመሥራት መብቶች እንዲያስከብር በያዟቸውና ባሰሟቸው መፈክሮች ጠይቀዋል፡፡ እነዚህ 500 የሚገመቱ የከተማው ነዋሪዎች ዜጎች ከመኖሪያና ከሥራ ቦታቸው ውጭ ለመንቀሳቀስ ወጥተው የተቸገሩበት ሁኔታ በመቀየር መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።ለዚህም ተገቢውን ጥበቃ ይደረግልን ብለዋል። አቶ ዮሐንስ ተሰማ የተባሉ ነዋሪ በሕገ ወጦች ሁከትና ግርግር በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞትና የአካል ጉዳት አሳስቧቸው በሰልፉ መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡ በዜጎች ላይ አድፍጠው ጥቃትየሚያደርሱ ናበከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭቶችን የሚቀሰቅሱ ወገኖች  እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ሌላዋ ሰልፉን የተካፈሉ የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ አለም ተገኝ መንግሥት ግጭቶች ለመፍታት ውይይት ዋነኛው መንገድ መሆኑን በማሳየትና የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይጠበቅበታል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የዚሁ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አዳነች በቀለ በበኩላቸው ''የሕግ የበላይነትን ማስከበር የሁላችንም ድርሻ ቢሆንም፤ የተደራጁ የጥፋት ኃይሎችን የማሰታገስ አቅምና ጉልበት ያለው መንግሥት ብቻ ነው'' ብለው እንደሚያምኑ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከል ''የተደራጁ የጥፋት ቡድኖችን እንቃወማለን!'' ፣''የሕግ የበላይነት ይከበር!''፣ ''ቂምና በቀል ይቅር!''የሚሉ ይገኙበታል፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም