ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ ስራ አስፈፃሚ ሾመ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ ስራ አስፈፃሚ ሾመ
አዲስ አበባ ግንቦት 28/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ዶክተር ንጉሴ ምትኩን ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ ሾመ።
ምክር ቤቱ በ6ኛው ልዩ ስብሰባው ዶክተር ንጉሴ ምትኩን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሹመትን በአራት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ዶክተር ንጉሴ ምትኩም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ የፈጸሙ ሲሆን ከዚህ በፊት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን በፕሬዝዳንትነት መምራታቸው ይታወቃል።
ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ስዩም መኮንን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።