የኢትዮጵያ ቡናና የመቐለ 70 እንደርታ ክለቦች ጨዋታ በዝግ እንዲካሄድ ተወሰነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ቡናና የመቐለ 70 እንደርታ ክለቦች ጨዋታ በዝግ እንዲካሄድ ተወሰነ
አዲስ አበባ ግንቦት 26/2011 የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሲያስታውቅ ኢትዮጵያ ቡና ውሳኔውን እንደማይቀበለው ገልጿል።
በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ እግር ኳስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናና መቐለ 70 እንደርታትናንትሊያካሂዱት የነበረው ጨዋታ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረውየክለቦቹ ጨዋታ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ከገቡ በኋላ ነበር የተሰረዘው።
ፌዴሬሽኑ ይህ ጨዋታ ነገ ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም/ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ በ9፡00 ሠዓት በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ሊቀመንበር መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ''ክለባችን ቡና የፈጸመው ምንም ጥፋት የለም'' ሲሉ ለኢዜአ ገልጸዋል።
''ጥፋት ሳንፈጽም ደግሞ ከሜዳችን ውጭ የምንጫወትበት ምክንያት የለም" በማለት የፌዴሬሽኑን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።
''መጀመሪያም የመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዳይገቡ የፈለግነውም ይህን ፍራቻ ነበር'' ሲሉም አክለዋል።