በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ2ሺህ500 በላይ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው ይመለሳሉ

83

ነቀምቴ ግንቦት 25/ 2011 በምዕራብ ወለጋ ዞን በመጪው ሳምንት ከ2ሺህ 500 ሺህ የሚበልጡ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ የዞኑ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት አስታወቀ ፡፡

ከዞኑ እስካሁን ከ50ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ተመልሰዋል።

የጽህፈት ቤቱ የፈንድና የመልሶ ማቋቋም የሥራ ሂደት አስተባባሩ  አቶ ግርማዬ ዳባ እንደገለጹት ተመላሾቹበቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል በዞን አዋሳኝ ወረዳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከነጆ ወረዳ የተፈናቀሉ ናቸው።

ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያዎችተፈናቃዮች መካከል እስካሁን 50ሺህ555 ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

እስካሁን ወደ ቄያቸው ያልተመለሱ በጊምቢ፣በነጆ፣በቅልጡ ከራና በመነ ሲቡ ወረዳዎች የሚገኙ

ተፈናቃዮችን ለመመለስም እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለተመላሾቹ በመደበው 7ነጥብ 9ሚሊዮን ብር የዘር ግዥ መጀመሩን አሰረድተዋል፡፡

በአሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉምዝ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ከዞኑ 54ሺህ ያህል ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም