ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና አዳማ ከነማ አንድ እኩል ተለያዩ

82

ግንቦት 24/2011 ዛሬ በመቀሌ ዓለም አቀፍ ስተድዮም በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና አደማ ከነማ እግር ኳስ ክለቦች እኩል አንድ ለአንድ ተለያዩ።

ዛሬ በመቀሌ ዓለም አቀፍ ስተድዮም በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና አደማ ከነማ እግር ኳስ ክለቦች እኩል አንድ ለአንድ ተለያዩ።

የአደማ ከነማ ከናን ማርክነህ በ90ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፤ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሰመረ ሃፍታይም በ93ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ጎል ቡድኑን ከመሸነፍ አድኖታል።

ጨዋታው በአቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ37 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ሲይዝ፤ አደማ ከነማ ደግሞ በ34 ነጥብ 11ኛ ደረጃን መያዙ ለማወቅ ተችሏል።

ጨወታው ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት ሁኔታ መካሄዱን ለመመልከት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም