ቀጥታ፡

በተለያዩ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል

አዲስ አበባ ግንቦት 23/2011 በአዲስ አበባ በተለያዩ ምርቶች ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር የዋጋ ጭማሪ በሚያባብሱ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ በተደራጀ አሰራር እርምጃ ሊወሰድ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስታወቁ።
የዋጋ ጭማሪውንና ህገወጥ ንግድንየሚቆጣጠር ግብረኃይል ሊቋቋም መሆኑም ተገልጿለል።

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር እንዳወቅ አብተው ጉዳዩን አስመልክተው ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲወያዩ እንደተናገሩት በከተማዋ በሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ ነዋሪውን በሚያማርሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ተገቢ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችና ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ 'እየተባባሰ መጥቷል' ብለዋል።

የዋጋ ጭማሪው በመዲናዋ ሰላማዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

እንደእርሳቸውገለጻተቋማት ችግሩን ለመፍታትበተናጠል እያደረጉት ያለው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል በማቋቋም ችግሩን ለመፍታት እየሰራ ነው።

በቀጣዩ ሳምንት ወደ ስራ የሚገባው ግብረ ኃይል ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመተባበር ምርቶችን በመጋዘናቸው በመደበቅ ሰው ሰራሽ እጥረትየሚፈጥሩ ህገወጥ ነጋዴዎችን ለህግ ለማቅረብ ይንቀሳቀሳል።

የግብይት ቦታዎችን በመለየትና ግብረ ኃይሉን በማሰማራት በእህል፣ በአትክልት፣ በብረትናሌሎች ምርቶች ላይ አላስፈላጊ የዋጋጭማሪ እንዲኖር በሚያደርጉ ዳላሎች ላይም "እርምጃ ይወሰዳል" ብለዋል።

ቁጥጥሩ ህጋዊ ደረሰኝ ሳይዙና ሳይሰጡ በሚሰሩ የእህል ወፍጮ ቤቶች፣ መጋዘኖች እንዲሁም የእህልና የአትክልት ገበያዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባው አስታውቀዋል።

ባለፉት 10 ወራት በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይተገቢያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 123 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም