የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ
አዲስ አበባ ግንቦት 21/2011 የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለብ ላደረገው አቀባበልና መልካም መስተንግዶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስጋናውን አቀረበ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ላደረገለት አቀባበልና መስተንግዶ ምስጋና አቀረበ።
ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም የ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚሪሊግ እግር ኳስ ጨዋታ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዴየም መካሄዱ ይታወሳል።
በእለቱባህርዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናገደበት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።
በዚህ ጨዋታ የባህርዳር ከተማእግር ኳስ ክለብ ለእንግዳው ክለብ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨስርስቲ ላደረገው አቀባበልና መልካም መስንግዶ ለባህርዳር ከተማ የምስገና ደብዳቤው ሰጥቶታል።
ጨዋታው ከመካሄዱ አራት ቀናት ቀደም ብሎ ለወልዋሎ እግር ኳስ ክለብ የማረፊያ ሆቴል በማዘጋጀትና የልምምድ ሜዳ በማመቻቸት ከበቂ ልምምድ በኋላ እንዲጫወቱ አድርገዋቸዋል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የእራት ግብዣ በማድረግም ባህርዳር በመልካም መስተንግዶው ተመስግኗል።
በዚህም ፌዴሬሽኑ ለባህርዳር ከተማ ከምስጋና ደብዳቤ ጋር ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።