የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ አዲስ የሥራ ኃላፊ ተሾመለት - ኢዜአ አማርኛ
የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ አዲስ የሥራ ኃላፊ ተሾመለት
ግንቦት20/2011ሱዳናዊው ፕሮፌሰር ሰይፈዲን ሃማድ አብደላ የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የሥራ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
ፕሮፌሰር ሰይፈዲን ሃማድ አብደላ አንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1979 የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከካርቱም ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
በኋላ በሱዳን መስኖ ሚኒስትር ውስጥ በባለሙያነት በመቀጠር ለበርካታ ዓመታት መሥራታቸውም ተጠቁሟል።
በመሃልም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው ኣታህ ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል።
ሱዳንን ጨምሮ በተለያዩ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችም በመምህርነት ጭምር በማገልገል በመስኩ የካበተ ልምድ እንዳላቸው ተጠቁሟል።
ይህንንም ተከትሎ የመነግሥታቱ ድርጅንት ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ለሥራቸው ዓለም አቀፍ እውቅና ሰጥቷቸዋል ተብሏል።
ይህንን አዲስ የሥራ ኃላፊነት ከመረከባቸው በፊትም የሱዳን የውኃ ኃብት የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ነበር።
በሥራ ዘመናቸውም በናይል ተፋሰስ አገራት የሚስተዋለውን የፖለቲካ መፋዘዝ መልሶ መቀስቀስ ላይ እሰራለው ብለዋል።
በተለይም ደግሞ ግብጽና ኤርትራን ወደ ኢኒሼቲቨቭ በቅድሚያ በማስገባት የፖለቲካ ሂደቱን ለማስቀጠል እሰራለው ነው ያሉት።
ኤርትራም በኢኒሼቲቩ ከነበራት የታዛቢነት ሚና ወጥታ ሙሉ በሙሉ በአባልነት አንድትሳተፍ እሰራለው ብለዋል።
ፕሮፌሰር ሰይፈዲን ከመነሻውም በናይል ተፋሰስ አገራት ወይም በምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት(ኢጋድ) አገራት መካከል ግጭት ጠፍቶ በኢኮኖሚው መስክ የሚተባበሩበት ስምምነት እንዲኖራቸው ሲጥሩ የነበሩ ባለሙያ ናቸው።
ኢ.አ.አ መጋቢት 2015 በግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን መካከል የተደረገው የሶስትዮሽ ስምምነት ከሚጠቀስላቸው ተግባራት አንዱ ነው።
የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ በተፋሰሱ የሚገኙ አስሩ አገራት በውሃውና የተፈጥሮ ሀብት ፍትሓዊ ተጠቃሚነት ላይ የሚመክሩበትና በቀጠናው የሚገጥሙ የምግብ፣ ውሃና ኃይል እጥረቶችን ተጋግዘው የሚወጡበት ስምምነት ነው።
ፕሮፌሰር ሰይፈዲን ሃማድ አብደላ የናይል ኢኒሼቲቭን ለመጪው ሁለት ዓመታት ይመራሉ።