አገር አቀፍ እናት ለሰላም እና ለእርቅ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አገር አቀፍ እናት ለሰላም እና ለእርቅ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ግንቦት 16/2011የሠላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኅበር "እናት ለሠላም እና ለእርቅ" በሚል መሪ ሃሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከሩ ነው።
መድረኩ በሃይማኖት አባቶችና አባገዳዎች ፀሎትና ምርቃት ነው የተጀመረው።
የተለያየ አቋም የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከክልሎች የተወጣጡ ወጣቶች፣ ጦማሪያንና የመብት ተሟጋቾችን በማሰባሰብ በእናቶች አማካኝነት የሠላም ጥሪ ለማቅረብ የተዘጋጀ ነው።
በመድረኩ የእናቶች ከቀዬአቸው መፈናቀል በአገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ እናቶች ለሠላምና እርቅ መስራት እንዳለባቸው ተነግሯል።
ሴት ሚኒስትሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎችን ጨምሮ የሠላም አምባሳደር እናቶች እና ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ሴቶችም እየተሳተፉ ነው።
የሠላም አምባሳደር እናቶች ከወራት በፊት ‘የሚስተዋለው የእርስ በርስ ግድያ፣ ግጭትና መፈናቀል አሰጋን፣ አስጨነቀን’ በማለት ሠላም እንዲሰፍንና የዴሞክራሲ ጅማሮው እንዳይደናቀፍ ለመማፀን ኢትዮጵያን መዞራቸው ይታወሳል።