የኮማንድ ፖስት መቋቋም የከተማው ሰላም ወደነበረበት እንዲመለስ አድርጓል- የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች

56

ሚዛንግንቦት 14/2011 የኮማንድ ፖስት መቋቋም የከተማው ሰላም ወደነበረበት እንዲመለስ ማድረጉን በደቡብ ክልል የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ 

የከተማዋአንዳንድ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት የኮማንድ ፖስቱን መቋቋም ተከትሎ በከተማውና አካባቢው ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ሰፍኗል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት ነዋሪዎች መካከል አቶ አህመድ መሐመድ ኮማንድ ፖስቱ ከመቋቋሙ በፊት ነዋሪው ስጋት ላይ እንደነበር አስታውሰው፣ መንግሥት የአካባቢውን ሰላም ለማረጋጋት የወሰደው እርምጃ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ዜጎች ሀብታቸው እንዲጠበቅና ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ ሰላምን የሚያደፈርሱ ወንጀለኞችን ተከታትሎ  እንዲቀጣ ጠይቀዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ ፋሲካ ኃይሌ ኮማንድ ፖስቱ በነጻነት እንድንቀሳቀስ አድርጎኛል ብለዋል።

የአካባቢውሰላምና ጸጥታ መንስዔዎችን አውቆ  መፍትሄ መስጠት እንደሚገባም አመልክተዋል።

አቶ ወሳ ካሳ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሰላም ዘላቂ የሚሆነው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በማድረግ በቅንጅት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስቱ የቆይታ ጊዜ መራዘሙ ተገቢ መሆኑን የገለጹት ነዋሪው፣ በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከሚያዝያ 21 ቀን 2011 ጀምሮ በካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም