በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልኡክ ጅቡቲ ገብቷል - ኢዜአ አማርኛ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልኡክ ጅቡቲ ገብቷል
ግንቦት 14/2011 በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የተመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ወደ ጅቡቲ ያቀናው በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ በቀብር ስነ~ስርዓት ላይ ለመገኘት መሆኑን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ዛሬ ማለዳ ጂቡቲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር አህመድ ካሚል አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጠናከረ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፥ ልማት እና ሰላም እንዲዳብር በሰጡት አመራር ይታወቃሉ።
የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆናቸው በስፋት ይነገርላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ~ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በኢፌድሪ መንግሥት ስም አስተላልፈዋል፡፡