ደቡብ ሱዳን 39 ኤምባሲዎችን ልትዘጋ ነው

63

ግንቦት13/2011 ደቡብ ሱዳን በውጪ ሃገራት የሚገኙ 39 ኢምባሲዎቿና በፋይናስ እጥረት ምክንያት ልትዘጋ መሆኑን ገለፀች፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማዊን ማኮል ጁባ በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎችዋ ለማስተዳደር አስቸጋሪ ሆኖባታል ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኤምባሲዎቹ በቅርብ ግዜ እንደሚዘጉም አስታውቀዋል፡፡

አገሪቱ ከዚህ ቀደም ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያለቻቸውን 40 ዲፕሎማቶች ከስራ ማሰናበትዋ ይታወሳል፡፡

በነዳጅ ምርት ላይ ኢኮኖሚዋ የተንጠለጠለው ወጣትዋ አገር ደቡብ ሱዳን በ2013 በጀመረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ምርትዋን መቀነሱ እና የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ይገለፃል፡፡
በአገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ ሙስና መስፋፋቱ እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የፋናንስቀውስ ማስከተሉንም ነው ዘ ኢስት አፍሪካ የዘገበው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም